Tuesday, October 31, 2017

Successful Marriage not divorce 2

አንድ በሚስቱ በጣም የተማረረ ባል ሳይኮሎጂስት ጋር ይሄዳል…
ሳይኮሎጂስት ፡- እሺ ጌታው ለመኖር ምንድ ነው የምትሰራው ?
ባል ፡- ባንክ ቤት ውስጥ ማናጀር ነኝ
ሳይኮሎጂስት ፡- እሺ ባለቤትህስ ምንድ ነው ምትሰራው ?
ባል ፡- እሷ ባክህ ምንም አትሰራም የቤት እመቤት ነች
ሳይኮሎጂስት ፡- ጠዋት ለቤተሰቡ ቁርስ ሚሰራው ማነው ?
ባል ፡- ሚስቴ ነቻ ምክንያቱም ምንም ስራ የለባትም..
ሳይኮሎጂስት ፡- ሚስትህ ጠዋት ከእንቅልፏ ስንት ሰአት ነው ምትነሳው ?
ባል ፡- ለሊት 11፡00 ሰአት አካባቢ ነው ምትነሳው ቁርስ ከመስራቷ በፊት ቤት ስለምታጸዳ ቀደም ብላ ነው ምትነሳው…..
ሳይኮሎጂስት ፡- ልጆችህ ትምህርት ቤት ሚሄዱት እንዴት ነው ?
ባል ፡- ሚስቴ ስራ ስለሌላት እሷ ነች የምትወስዳቸው
ሳይኮሎጂስት ፡- ልጆችህን ትምህርት ቤት ከወሰደደች በኋላ ምን ትሰራለች ?
ባል ፡- ከወሰደቻቸው በኋላ ያው ስራ ስለሌለባት ወደ ገበያ ሄዳ ምሳ የሚሰራበትን ነገር ትገዛዛና ምሳ ከሰራች በኋላ ልብስ ታጣጥብና እረፍት ታረጋለች በቃ ምንም ምትሰራው ስራ የላትም
ሳይኮሎጂስት ፡- አንተ ማታ ከስራ ስትመለስ ምን ታረጋለህ ?
ባል ፡- እኔ ስራ ደክሜ ስለምገባ በቃ ሻወር እወስድና ረጋ ብዬ ከልጆቼ ጋር እቀመጣለሁ
ሳይኮሎጂስት ፡- የዛኔ ሚስትህ ምን ትሰራለች ?
ባል ፡- ለቤተሰቡ ራት ታቀርብና እቃ ታጣጥብና ልጆቹን አስተኝታ ወደ እንቅልፍ ትሄዳለች
ሳይኮሎጂስት ፡-እሺ ከአንተና ከሚስትህ ማን በጣም የሚሰራ ይመስልሃል የሚስትህ ውሎ ከንጋቱ 11 ሰአት የጀመረ እስከ ማታ ድረስ የሚቀጥል ነው፡፡ ታዲያ ይሄንን ነው ስራ ስለሌለባት የምትለው !!!! አዎ በርግጥ የቤት እመቤት ለመሆን ትምህርት ቤት ገብቶ ሰርተፍኬት መቀበል ላያስፈልገው ይችላል፡፡ ግን በሕይወታችን ውስጥ የነሱ አስተዋጽኦ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
Appreciate your wife's because their sacrifices is uncountable.
ስለ ሴቶቻችን…..
• ፀጥ ስትል ብዙ ሚሊዮን የሚሆኑ ሃሳቦችን እያሰበች እያብሰለሰለች መሆኑን ይግባህ፡፡
• አፍጣ ስታይህ ለምን እንደዚ እንደምትወድህ እና ይህን ሁሉ መስዋትነትን እንደምትከፍልልህ እያሰበች ነው፡፡
• አብሬህ እቆማለው ስትልህ ማዕበል እንኳን ቢመጣ አልንቀሳቀስም ማለቷ ነው፡፡
• አትጉዳት ወይም በተሳሳተ መንገድ አታስባት….አንተ ስትራብ ተርባ ስትቸገር ተቸግራ ስትራቆት ተራቁታ ገበናህን ሸፍና የምትኖረው ሚስትህ የልጆችህ እናት ሚስትህ ናት፡፡ አረ እውነታውን ልንገርህ ሚስትህ ማለት የቤትህ ብርሀን ናት።
ስለዚህ አክብራት ውደዳት ፍቅርን ስጣት፡
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»

Successful Marriage not divorce 1

ውዷ እህቴ *ለባልሽ* 17 ነገሮች!!

1/ ግትርነትን ተጠንቀቂ፣ መልካም ትዳርን ያናጋል።

ባልሽን ወንድነቱን የተፈታተንሽው ይመስለዋል።

2/ ሙግትነትን ተጠንቀቂ፣ ሙግት ትልቅ በሽታ ነው።

3/ ሌሎችን አትመልከች እንደቤትሽ አብቃቅተሽ መኖር ልመጂ።

4/ አቀባበልሽን አሳምሪ፤ ዋናው የፍቅር ማጠንከሪያ ነው። (ከፍትፍቱ ፊቱ)

5/ ለስለስ ያለ ባህሪ ይኑርሽ። ተወዳጅ ያደርግሻልና።
ጥሩ ስራ ስታይበት በደስታ ግለጪለት።

6/ ያየሽውንና የሰማሽውን ሁሉ አታውሪለት ወንድ ብዙ ወሬ አይወድምና።

ሚስጥሩን ጠብቂለት በሁሉም በኩል ሚዛናዊ ሁኚ ዘውድ የተጫናት ንግስት ያደርግሻል።

7/ በሱ በኩል በሰጠሽ ፀጋ አላህን አመስግኚ።

8/ ምንግዜም ውበትሽን ጠብቂ። አንቺ ከባልሽ ብዙ ነገሮችን እንደምትፈልጊ እሱም ካንቺ ይሻል! ብዙ ጊዜ ሴት እቤቷ በምትውልበት ቀን የማድ-ቤት ስራ ይዞሽ ትውይ ይሆናል ባለቤትሽ ወደቤት ሲመጣ ተዘጋጅቶ የሚጠብቀው የሚበላ የሚጠጣ ነገሮች ብቻ ናቸው።

የሚበላና የሚጠጣ እኮ እውጪም አይጠፋ እህቴ ነው ወጭ ለመቀነስ አይደለም ለሱ ከምግቡም ከምኑም ይልቅ ያንቺ ታጥቦና ተኩሎ ለሱ ከምንም በላይ ነው።

9/ ብዙ ግዜ ልብ የማንላቸው ነገሮች አሉ። ፈጅር ላይ ከመኝታ ተነስተን ልብስ ለብሰን የሆነ ነገር ቁርስ ሰርተሽ ባለቤትሽ ለስራ ከወጣ ቡሃላ አንቺም
በቤቱ ስራ ጎንበስ ቀና ስትይ ያንኑ የበለበሽውን ልብስ ሳታወልቂው ማታ ተመልሶ ይመጣል።

ያኡክቲ ይሄ አግባብ አይደለም። የበለጠ ውብ ሆነሽ ቆይው ባለቤትሽ አንቺን ሲያይሽ እንዲደሰት አርጊው።

10/ ወንድ ልጅ በውበት እንደሚማረክ እወቂ። እናም ባለቤትሽ ሌላውብ እንዳያይ አንቺ ውብ ሁኚ እራስሽን ጠብቂ።

11/ ሀዘንም ጭንቀትም ቢሆን ያንቺ እንደዛ መሆን ሁሉን ያቀልለታል። አስታውሽ የሰሃባዋን ኡሙ ሰለይማን ረ.ዓ ታሪክ የልጇን እሬሳ አስተኝታ ለባሏ እንዴት ውብ ሆና እንደጠበቀችው።
አየሽ እህቴ የባል ሀቅ እስከዚህ ድረስ ነው።

12/ ከማግባትሽ በፊት ውብ ትሆኚ አልነበር አሁን ቤትሽን ብቻ ማስዋብ አይሁን ስራሽ አንቺም ውብ ሁኚ። ከበፊቱ ውብ መሆኛሽ አሁን ነው።
13/ ሀላፊነት አለብሽ ለባልሽ ማራኪ የመሆን።

14/ ቤትሽን (ትዳርሽን) የበለጠ የሚያደምቀው በቁሳቁስ አይደለም። አንቺ ባልሽን ስታስደስቺ ነው።

15/ ያጠፋውን ነገር ብቻውን ቀስ ብለሽ ንገሪው።

ሀቁን ጠብቂ ተበሳጭቶ ሲገባ አረጋጊው።
16/ ደስተኛ በሆናችሁበት ሰዓት እንደምቶጂውም ንገሪው።

17/ ምንግዜም በዱአሽ እንዳትረሽው።
ለዲኑም እንዲጠነክር እርጂው።

ያገባችሁ አላህ ጥሩ ሚስት ያድርጋችሁ ያላገባችሁ አላህ ጥሩ ትዳር ይወፍቃችሁ።

Thursday, October 12, 2017

Inter country Adoption in Ethiopia

የውጭ አገር ጉዲፈቻ የተፈጥሮ ቤተሰብ ፍቅርና እንክብካቤን ሙሉ በሙሉ የማይተካና ከዚህ ቀደም በጉዲፈቻ ወደ ውጭ አገራት የሄዱ ህፃናት ላይ የማንነት ቀውስ በማስከተሉ፣ ይህን አሠራር የሚፈቅደው የሕግ ድንጋጌ ከቤተሰብ ሕጉ እንዲሠረዝ መንግሥት ወሰነ።

http://new.ethiopianreporter.com/article/1881